ወደ ሀዋሳ ከነማ ማምራት በመፈለጉ ደደቢትን እንደሚለቅ ሲጠበቅ የነበረው በረከት ይስሃቅ ወደ ሃዋሳ ከነማ ማምራቱ እውን ሆኗል፡፡
በረከት በደደቢት 1 አመት ቀሪ ኮንትራት የነበረው ሲሆን ሀዋሳ ከነማ የቀድሞ አጥቂውን ለማግኘት ፍላጎት የነበረው በመሆኑ ለደደቢት ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ሰማያዊው ጦርም ጥያቄያቸውን መቀበሉን ከክለቡ ህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ደደቢት ተጫዋቹን ለመልቀቅ የውል ማፍረሻ 700ሺህ ብር መቀበሉንም ጨምሮ ገልጧል፡፡
በረከት ይስሃቅ በአሁኑ ሰአት የሚገኘው ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር በባህርዳር ሲሆን በቅርቡ ለሀዋሳ ከነማ ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡