ቅዱስ ጊዮርጊስ አምስተኛ የውጪ ተጫዋች አስፈረመ

ባለፈው ሳምንት የአራት የውጪ ተጫዋቾችን ዝውውር ያጠናቀቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋናዊው ተከላካይ ኤድዊን ፍሪምፖንግ ማንሶን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል። 

በክረምቱ አበባው ቡታቆን የለቀቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ በግራ ተከላካይ ስፍራ ላይ መሐሪ መናን ብቻ ይዞ የነበረ ሲሆን የፍሪምፖንግ ዝውውር በቦታው ያለውን አማራጭ የሚያሰፋለት ይሆናል። 

የ24 ዓመቱ ጋናዊ ከዚህ ቀደም በሀገሩ ክለቦች አሻንቲ ኮቶኮ እና ሊበርቲ ፕሮፌሽናልስ ተጫውቷል። 

በሀገራችን ክለቦች የመስመር ተከላካይ ማስፈረም እምብዛም ያልተለመደ ቢሆንም አምና መቐለ ከተማ አቼምፖንግ አሞስን፣ ዘንድሮ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቀኝ ተከላካዩ ኢሲፎ ቦውራሀና እና የግራ ተከላካዩ ፍሪምፖንግን ፣ ሀዋሳ ከተማ ደግሞ ያኦ ኦሊቨር ኩዋኩን አስፈርመዋል።