የአሰልጣኞች አስተያየት| መቐለ 70 እንደርታ 1-0 ወልዋሎ

በመቐለ 70 እንደርታ አሸናፊነት ከተጠናቀቀው የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

“ጨዋታውን ተቆጣጥረን አሸንፈን ወጥተናል” ገ/መድህን ኃይሌ

ስለ ጨዋታው

የደርቢ ጨዋታ ከባድ ነው፤ ውጥረት ይበዛዋል። ይህ ጨዋታም ከባድ እና ውጥረት የበዛበት ነበር። ሆኖም ጨዋታውን ተቆጣጥረን አሸንፈን ወጥተናል። እንደነበርን ብልጫ የጎል ልዩነቱ ከአንድ በላይ መሆን ይገባው ነበር። ግን በአጠቃላይ አሸንፈን ስለወጣን ደስ ብሎኛል። ጨዋታው ሰላማዊ መሆኑ ራሱ ደስ ይላል።

ስለታየው ስፖርታዊ ጨዋነት

ሜዳ ውስጥ ስለ ስፖርት እና ስፖርት ብቻ ትኩረት መደረግ አለበት። አንዳንዴ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሚታዩት እንቅስቃሴዎች መጥፋት አለባቸው።

“የተሻሉ ስለ ነበሩ አሸንፈውናል” ዮሐንስ ሳህሌ

ስለ ጨዋታው

የተሻሉ ነበሩ አሸንፈውናል። በተለይ የመጀመርያው አጋማሽ ተጫዋቾቻችን አፈግፍገው ምንም የሰራነው ነገር የለም። በዚህም በአጋማሹ ግብ አግብተው አሸንፈውናል። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ነገር ለማድረግ ሞክረናል፤ ግን የተሻሉ እነሱ ነበሩ። በጭንቅላት ዝግጅት በልጠውናል፤ ስለዚህ አሸንፈውናል። ከዕረፍት በፊት በብዛት ወደ ጎል እንኳ ባይሄዱ ኳሱን በመያዝ እና የኛን ኳስ በማሳደድ ውጣታማም ባይሆኑ ከጎሉ ውጭ።

ጎሉ መቶ በመቶ የግብ ጠባቂያችን ስህተት ነው። አማኑኤል ለግቡ መቆጠር የሚገባውን እውቅና ነው የምሰጠው። ሆኖም ግን ጎሉ የተቆጠረው መቶ በመቶ የግብ ጠባቅያችን ስህተት ነው።

መቐለዎች የመጫወት እና የማሸነፍ ፍላጎት ስለነበራቸው፤ የደጋፊው ኃይልንም ተጠቅመው አሸንፈውናል፤ በማንም አናሳብብም።

ስለ ቀጣይ

ለሚቀጥለው ጨዋታ ተዘጋጅተን እንመጣለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ