መብረቅ የጤና ቡድን ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አድርጓል

ከተቋቋመ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረው የካዛንቺሱ መብረቅ የጤና እግርኳስ ቡድን ለአቅመ ደካማ የማኅበረሰብ ድጋፍ አድርጓል።

ከተመሰረተ ሀምሳ ሁለት ዓመታት የሞላው እና ከአርባ እስከ ሀምሳ እድሜ ክልል የሚገኙ ግለሰቦችን በአባልነት ያቀፈው የካሳንችሱ መብረቅ የጤና እግር ኳስ ቡድን በዛሬው ዕለት ከ50 ለሚበልጡ አባወራ እና እማወራዎች የተለያዩ ምግብ እና የምግብ ግብዓቶችን አበርክተዋል። በአዲስ አበባ ጤና ስፖርት ማኅበር ስር ተመዝግቦ የሚወዳደረው ቡድኑ ከዚህ ቀደምም በካዛንችስ እና አካባቢዋ ያሉ አቅመ ደካሞችን በመርዳት እንደሚታወቅ የተገለፀ ሲሆን አባላቱም በአብዛኛው በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ በተጨዋችነትና አሁን በአሰልጣኝነት እያገለገሉ ያሉ ናቸው። ከነዚህም መካከል አብርሀም መብራቱ፣ ጳውሎስ ጌታቸው፣ አሳምነው ገ/ወልድ ያሉ አባላት በቦታው በመገኘት ይህን ስጦታ አበርክተዋል፡፡

በአለማችን የተከሰተው ወረርሽኝ እስኪጠፋ በቀጣይም ይህንኑ ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የቡድኑ አባል እና የቀድሞው የንግድ ባንክ አሰልጣኝ ሲሳይ ከበደ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ