ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ቡና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረው ጨዋታ አሰላለፍ ታውቋል።

ከሀገሪቱ ትልቅ ቡድኖች ጋር በተከታታይ በመጫወታቸው በጊዮርጊስ ላይ ያሳዩትን አቋም ለማስቀጠል እና ቡና ከኋላ መስርቶ እንደሚጫወት ስለሚያውቁ ከፊት ጫና አሳድረው ጎሎችን ለማግኘት እንዳሰቡ ያጠቆሙት አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አቻ ሲለያዩ ከተጠቀሙበት ቡድን የሦስት ተጨዋቾች ቅያሪ አድርገዋል። በቅያሪዎቹ ቅጣት ላይ የሚገኘው ፈቱዲን ጀማልን በግርማ በቀለ ፣ ዳዊት ተፈራን በያስር ሙገርዋ እንዲሁም አዲሱ አቱላን በተመስገን በጅሮንድ በመለወጥ በሦስቱም የመጫወቻ ቦታዎች ላይ ማስተካከያ አድርገዋል።

ከባህር ዳሩ የ 2-2 ጨዋታ የ ተጫዋቾች ሦስት ለውጥ ያደረጉት አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በበኩላቸው ተጋጣሚዎች ለቡና የሚቀርቡበትን መንገድ የሚታወቅ እንደሆነ ለዛም መዘጋጀታቸውን እና የሚሰሯቸውን ስህተቶች በመቀነስ ውጤት ይዘው ለመውጣት እንደሚጥሩ ተናግረዋል። አሰልጣኙ ባደረጓቸው ለውጦች ቅጣት ላይ የሚገኘው ተክለማሪያም ሻንቆ በአቤል ማሞ ሲተካ ሬድዋን ናስር እና አቤል ከበደ በአማኑኤል ዮሃንስ እና ሚኪያስ መኮንን ቦታ ጨዋታውን ይጀምራሉ።

ጨዋታውን ፌደራል ዳኛ ባህሩ ተካ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።

የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ሲዳማ ቡና

1 ፍቅሩ ወዴሳ
3 አማኑኤል እንዳለ
19 ግርማ በቀለ
24 ጊት ጋትኮች
32 ሰንደይ ሙቱኩ
16 ብርሀኑ አሻሞ
6 ዮሴፍ ዮሐንስ
10 ዳዊት ተፈራ
11 አዲሱ አቱላ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ
27 ማማዱ ሲዲቤ

ኢትዮጵያ ቡና

99 አቤል ማሞ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
11 አሥራት ቱንጆ
15 ሬድዋን ናስር
13 ዊልያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
17 አቤል ከበደ
10 አቡበከር ናስር
25 ሀብታሙ ታደሰ


© ሶከር ኢትዮጵያ