በሴካፋ ያንፀባረቀው ኤርትራዊ ተጫዋች ለባህር ዳር ከተማ ፈርሟል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ላይ ሦስት ጎሎችን ያስቆጠረው የኤርትራው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ለጣና ሞገዶቹ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።

በቀጣይ የውድድር ዘመን ተጠናክሮ ለመቅረብ እጅግ በዝውውር ገበያው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ባህር ዳር ከተማዎች በትናንትናው ዕለት ለሴካፋ ውድድር በከተማቸው የሚገኘውን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ዓሊ ሱሌማን ለማስፈረም ድርድር ሲያደርጉ እንደነበር ሰምተናል። የክለቡ አመራሮች በትናንትናው ዕለት ከተጫዋቹ ጋር ባደረጉት ድርድርም መስመር የያዙ ጉዳዮች እንደተፈጠሩ የሰማን ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ተጫዋቹ የሁለት ዓመት ፊርማ መፈረሙን ለማወቅ ችለናል።