ፋሲል ከነማ ከአሰልጣኙ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

በወቅታዊ ውጤት እየተቸገረ የሚገኘው የዓምናው የሊጉ ቻምፒዮን ከአሰልጣኙ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

ያለፉትን ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ዐፄዎቹን የተረከቡት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ቡድኑን የሊጉን ዋንጫ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ እንዲያነሳ ማስቻላቸው ይታወቃል። ሆኖም ዘንድሮ ቡድኑ በወቅታዊ ውጤት ማጣት መቸገሩን ተከትሎ በዛሬው ዕለት የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ ባደረገው አሰቸኳይ ስብሰባ ከአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር በስምምነት ለመለያየት ወስኗል። በዚህም ሰዓት ክለቡ ባረፈበት ሆቴል በአዳማ ከተማ ለአሰልጣኝ ስዩም አሸኛኘት እየተረገላቸው እንደሆነም አውቀናል።

እንደምክንያት የተወሰደው የቡድኑ ወቅታዊ የውጤት ማጣት እንደሆነ ታውቋል። ክለቡን በቀጣይነት በምክትል አሰልጣኞቹ የሚመራ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ክለቡ ቀጣዩን አሰልጣኝ እንደሚያሳውቅ ሰምተናል።