ሀዋሳ ከተማ የተጨማሪ ተጫዋች ዝውውር ፈፅሟል

ሀዋሳ ከተማ አንድ አጥቂ ሲያስፈርም የሦስት ነባር ተጫዋቾችን ኮንትራትም አራዝሟል።

\"\"

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ጠንካራ ተሳትፎን በማድረግ የሚታወቀው ሀዋሳ ከተማ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ከሰሞኑ የሰባት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ያጠናቀቀ መሆኑ እና የአምስት ነባሮችን ውል ማደሱ ይታወሳል። ክለቡ በዛሬው ዕለት ደግሞ የአንድ አዲስ ተጫዋችን ዝውውር ሲቋጭ የሦስት ነባሮችን ውል አድሷል።

አጥቂዋ ሰላማዊት ጎሳዬ የሀዋሳ ስምንተኛዋ ፈራሚ ሆናለች። ከአርባምንጭ ከተማ የእግር ኳስ ህይወቷን የጀመረችው አጥቂዋ ያለፉትን ተከታታይ ዓመታት ደግሞ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ካሳለፈች በኋላ ቀጣይ መዳረሻዋ እንስት ኃይቆቹ ሆኗል።

\"\"

ክለቡ የሦስት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ኮንትራትም አድሷል። ከሰሞኑ የሴካፋ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ ላይ በ5 ግቦች ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆና ያጠናቀቀችው እና ከሀዋሳ የታችኛው ቡድን የተገኘችው አጥቂዋ እሙሽ ዳንኤልን ጨምሮ አጥቂዋ ህይወት ቶማስ እና ግብ ጠባቂዋ እልልታ ጌታቸው ውል ያራዘሙ ተጫዋቾች ሆነዋል።

\"\"