​የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ተጀምሯል

የኢትዮጵያ ከ17 አመት የ2010 የውድድር ዘመን ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጀምሯል። በሁለት ምድብ ተከፍሎ የሚደረገው እና በድምሩ 14 ክለቦችን የሚያሳትፈው ውድድር ከየምድቡ አንድ አንድ ጨዋታ ተደርጎበታል። 

ምድብ ሀ

ሀዋሳ ከተማ 3-2 አዳማ ከተማ

እጅግ ጠንካራ ፉክክር በተስተናገደበት እና ሁለቱም ክለቦች ማራኪ እንቅስቃሴን ባደረጉበት ጨዋታ የአምናው ቻምፒዮን ሀዋሳ ከተማ በሜዳው አዳማ ከተማን አሸንፏል። በመጀመሪያው አጋማሽ ሙሉ የጨዋታ ብልጫ የነበራቸው አዳማዎች ቢሆኑም ሀዋሳ ከተማ ግብ በማስቆጠሩ ቀዳሚ ነበሩ።

ሀዋሳ መስፍን ታፈሰ በ11ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ሀዋሳዎች ቀዳሚ መሆን ቢችሉም አዳማዎች በፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ በ27 እና 28ኛው ደቂቃ ላይ በሙአዚ ሙህዲን እና ንጋቱ ኃይሉ አማካኝነት አከታትለው ባስቆጠሯቸው ጎሎች ቀዳሚ በመሆን የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።

በሁለተኛው አጋማሽ የበላይ መሆን የቻሉት ሀዋሳዎች 49ኛው ደቂቃ ላይ በወንድወሰን ኃይሉ አማካኝነት አቻ መሆን ሲችሉ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሁለት ደቂቃ ሲቀረው ሙሉቀን ታደሰ በግንባሩ አስቆጥሮ ሀዋሳ ሙሉ ሶስት ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎታል፡፡

ምድብ ለ

ወላይታ ድቻ 2-2 አፍሮ ፅዮን 

ሶዶ ስታዲየም ላይ በተደረገው የምድብ ለ ጨዋታ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። ለወላይታ ድቻ ከድር ዳንሳ እና አዛርያት ሳሙኤል ሲያስቆጥሩ ለአፍሮ ፅዮን ሮቤል ሰለሞን ሁለቱንም ጎሎች አስቆጥሯል።

ቀጣይ ጨዋታዎች

ምድብ ሀ

ዕሁድ ጥር 13 ቀን 2010

5:00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ከሲዳማ ቡና (ኤሌክትሪክ ሜዳ)

5:30 ማራቶን ከ ደደቢት (ማራቶን)

አራፊ ቡድን – መከላከያ

ምድብ ለ

ዕሁድ ጥር 13 ቀን 2010

5:00 ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮጵያ ቡና (መድን ሜዳ)

5:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢ/ወ/ስ/ አካዳሚ (-24 ሜዳ)

አራፊ ቡድን – ዱከም ከተማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *