የኮንፌድሬሽን ዋንጫ ድልድል ቋት ይፋ ተደርጓል

የቶታል ካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የቋት ድልድል ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡ ካፍ አራት ቋቶችን ነገ ለሚወጣው የኮንፌድሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ድልድል ለመዘጋጀታቸው በተረፈ የጥሎ ማለፍ ድልድሉ የሚወጣበትን ህግም አስታውቋል፡፡

በቻምፒየንስ ሊጉ ሲወዳደሩ የነበሩ 16 ቡድኖች ተሸንፈው ወደ ምድብ ማምራት ባለመቻላቸው ወደ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ወርደዋል፡፡ ከነዚህ ቡድኖች ውስጥ የኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ይገኝበታል፡፡ ኢትዮጵያ በሁለተኛው የአፍሪካ የክለቦች ውድድር ላይ ሁለት ቡድኖቿ ወደ ምድብ ለመግባት ይፋለማሉ፡፡ በ2013 ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ምድብ ካመራ በኃላም የትኛውም የኢትዮጵያ ክለብ ይህንን ስኬት መድገም አልቻለም፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቋት 1 ላይ ሲካተት ዛማሌክን የረታው ወላይታ ድቻ በቋት 4 ላይ ይገኛል፡፡ 32 ቡድኖች ወደ ምድብ ለመግባት የሚፋለሙ ይሆናል፡፡

ቋቶቹ እና የተካተቱት ቡድኖች እነዚህን ይመስላሉ

ቋት 1– አል ሂላል (ሱዳን)፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኢትዮጵያ)፣ ኤኤስ ቪታ ክለብ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)፣ ዛናኮ (ዛምቢያ)

ቋት 2– ዩኒየንስ ስፖርቲቭ መዲና ደ አልጀር (አልጄሪያ)፣ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ (ደቡብ አፍሪካ)፣ አል ሂላል ኦብዬድ (ሱዳን)፣ ኢኒየምባ (ናይጄሪያ)

ቋት 3– አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር)፣ ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን)፣ ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ)፣ ዊልያምስቪል (ኮትዲቯር)፣ አዱና ስታርስ (ጋና)፣ ጎር ማሂያ (ኬንያ)፣ ዩዲ ሶንጎ (ሞዛምቢክ)፣ ማውንቴን ኦፍ ፋየር ሚኒስትሪ (ናይጄሪያ)፣ ፕሌቶ ዩናይትድ (ናይጄሪያ)፣ ራዮን ስፖርት (ሩዋንዳ)፣ ጄኔሬሽን ፉት (ሴኔጋል)፣ ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ)

ቋት 4– ሲአር ቤሎዝዳድ (አልጄሪያ)፣ ላ ማንቻ (ኮንጎ ሪፐብሊክ)፣ ካራ ብራዛቪል (ኮንጎ ሪፐብሊክ)፣ አል መስሪ (ግብፅ)፣ ዲፖርቲቮ ኒፋንግ (ኤኳቶሪያል ጊኒ)፣ ወላይታ ድቻ (ኢትዮጵያ)፣ ፎሳ ጁኒየርስ (ማዳጋስካር)፣ ጆሊባ (ማሊ)፣ ሬኔሳንስ በረካን (ሞሮኮ)፣ ራጃ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ)፣ ኮስታ ዶ ሶል (ሞዛምቢክ)፣ አክዋ ዩናይትድ (ናይጄሪያ)

ቋት 1 ላይ የሚገኙ አራት ቡድኖች ቋት 4 ላይ ከሚገኙ አራት ቡድኖች ጋር በእጣ ድልድል ይደርሳቸው፡፡ ቋት 2 ላይ ያሉት አራት ቡድኖች በተመሳሳይ ቋት 3 ላይ ካሉ አራት ቡድኖች ጋር በእጣ ይደለደላሉ፡፡ ቀሪዎቹ 8 ቋት 3 ላይ የሚገኙ ቡድኖች ከቀሪዎቹ 8 የቋት 4 ቡድኖች ጋር ይገናኛሉ፡፡ በተመሳሳይ ቋት ላይ የሚገኙ ቡድኖች በፍፁም አንድ ላይ አይደለደሉም፡፡ የኮንፌድሬሽን ዋንጫ አንደኛ ዙር ላይ የነበሩ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ ያደርጋሉ፡፡ በዚህም ወላይታ ድቻ የመጀመሪያውን ጨዋታ ከሜዳው ውጪ የሚያርግ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንፃሩ በሜዳው ያደርጋል፡፡

የቋት ድልድሉ የተደረገው ክለቦች በአፍሪካ የክለቦች ውድድር ባስመዘገቡት የአምስት አመት ውጤት ነው፡፡ ቋት 1 ያሉት አራት በከፍተኛ ደረጃ ላይ የተገኙ ከቻምፒየንስ ሊጉ የወረዱ ክለቦች ሲሆኑ በቋት 2 ላይ በከፍተኛ ደረጃ ላይ የተገኙ አራት የኮንፌድሬሽን ዋንጫ አንደኛ ዙር ያለፉ ክለቦች ተቀምጠዋል፡፡ ቀሪ 12 ከቻምፒየንስ ሊጉ የወረዱ ክለቦች ቋት 3 ላይ ሲገኙ ሌሎች 12 ቡድኖች ደግሞ ቋት 4 ላይ ይገኛሉ፡፡

የቻምፒየንስ ሊግ ምድብ ድልድል ቋቶች

ቋት 1 – ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)፣ አል አሃሊ (ግብፅ)፣ ኤትዋል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ)፣ ዋይዳድ አትሌቲክ ክለብ (ሞሮኮ)

ቋት 2 – ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ)፣ ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ)፣ ኤስፔራንስ ስፖርቲቭ ደ ቱኒዝ (ቱኒዚያ)፣ ኢኤስ ሴቲፍ (አልጄሪያ)

ቋት 3 – ሞውሊዲያ ክለብ ደ አልጀር (አልጄሪያ)፣ ካምፓላ ሲቲ ካውንስል ኦቶውሪቲ (ዩጋንዳ)፣ ሆሮያ አትሌቲክ ክለብ (ጊኒ)፣ ምባባኔ ስዋሎስ (ስዋዚላንድ)

ቋት 4 – ፕሪሜሬ ደ አውጉስቶ (አንጎላ)፣ ታውንሺፕ ሮለርስ (ቦትስዋና)፣ ዲፋ ኤል ጃዲዳ (ሞሮኮ)፣ ኤኤስ ፖርት ቶጎ (ቶጎ)

የምድብ ድልድሉ ነገ በሪትዝ ካርልተን ሆቴል ካይሮ ላይ ምሽት 12፡00 ላይ ይደረጋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *