የኢትዮጵያ ዋንጫ ዘንድሮ አይደረግም

የ2012 የኢትዮጵያ ዋንጫ (ጥሎ ማለፍ) ውድድር ዘንድሮ እንዳይደረግ ክለቦች በድምፅ ብልጫ ወሰኑ፡፡

የዘንድሮው የውድድር ዓመት የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር እንደማይካሄድ ክለቦች ዛሬ በአዳማ ኤክስኪውቲቭ ሆቴል እየተደረገ ባለው ውይይት ላይ በድምፅ ብልጫ ወስነዋል፡፡ ውድድሩ ክለቦች ለውውድሩ ትኩረት እየሰጡት ባለምጣታቸው እና ለተጨማሪ ወጪ እየዳረጋቸው በመሆኑ የተነሳ ሊሰረዝ ችሏል። በዚህም መሠረት የጥሎ ማለፉን ውድድር በተመለከተ በደንቡ ላይ ሰፍረው የነበሩ አንቀፆች በሙሉ የተሰረዙ ሲሆን በፕሪምየር ሊጉ አንደኛ የሚወጣው ቡድን በቻምፒዮንስ ሊግ ሲሳተፍ የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር በመቅረቱ በሊጉ ሁለተኛ የወጣው ክለብ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡

በአንዳንድ አስገዳጅ ምክንያቶች ሳይካሄዱ ከቀሩባቸው ጥቂት ጊዜያቶች በቀር ከ1937 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ይህ ውድድር ከ2004 በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የማይደረግ ይሆናል። በወቅቱ ደደቢት ሁለተኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቅ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ መሳተፉ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ