አዲሱ የባህር ዳር ከተማ የሴቶች ቡድን በርከት ያሉ ተጨዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

ባህር ዳር ከተማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘንድሮ የእንስቶች ቡድን በማቋቋም ወደ ውድድር ለመግባት ዝግጅቱን እያደረገ ይገኛል።

ከቀናት በፊት ሰርካዲስ እውነቱን አሰልጣኝ አድርገው የቀጠሩት ባህር ዳር ከተማዎች ለሚሳተፉበት የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ውድድር ዝግጅታቸውን በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም እያደረጉ ይገኛሉ። አዲስ የተመሰረተው ቡድኑ በአሰልጣኝ ሰርካዲስ እየተመራ 25 ወጣት ተጨዋቾችን ከተለያዩ ክለቦች እና ፕሮጀክቶች በማምጣት የዓመታዊ ውድድሩን መጀመር እየተጠባበቀ ይገኛል።

ክለቡ ወደ ስብስቡ የቀለቀላቸው ተጨዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-

ራሄል ኢያሱ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ዳሳሽ ሰውአገኝ(ድሬዳዋ ከተማ)፣ መሠረት ዮናስ (አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ)፣ ቤተልሄም ግዛቸው (አርባ ምንጭ ከተማ)፣ ጥሩወርቅ ወዳጆ (ጥረት ኮርፖሬት)፣ ሊዲያ ጌትነት (ጥረት ኮርፖሬት)፣ ትግስት ወርቄ (ጥረት ኮርፖሬት)፣ ቤዛዊት መንግስቴ (ጥረት ኮርፖሬት)፣ ዘቢደር ሙሉ (ጥረት ኮርፖሬት)፣ ዮርዳኖስ አረጋ (ጥረት ኮርፖሬት)፣ አማሩ አብተው (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ይፍቱስራ ባለው (ኢ.ወ.ስ አካዳሚ)፣ ባንቺአየሁ ደመላሽ (ኢ.ወ.ስ አካዳሚ)፣ መንደሪን ታደሠ (አሰላ አካዳሚ)፣ ዝናሽ ደሳለኝ (አሰላ አካዳሚ)፣ ማስተዋል ጌጡ (ፋሲል ከነማ)፣ ሰብለወንጌል ወዳጆ፣ ዝናሽ ብርሀኑ፣ አደራ አናጋው፣ መማር ለቻለ፣ ፋሲካ ውበት፣ ፋሲካ ክንዴ፣ ኤልሻዳይ ይስሀቅ፣ ጥሩዓለም  ደሳለኝ፣ አፀደ በላይነህ

*ስማቸው አጠገብ ክለብ ያለተገለፀው ከፕሮጀክት የተገኙ ተጨዋቾች ናቸው።

አሰልጣኝ ሰርካዲስ እውነቱ ከ25ቱ ተጨዋቾች በተጨማሪ የምክትል እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ለመሾም እንቅስቃሴ መጀመሯ ተሰምቷል። በዚህም ከአሰልጣኟ (ሰርካዲስ) ጋር ለዋና አሰልጣኝነት ሲወዳደር የነበረው እውነቱ ታለ እና በጥረት ኮርፖሬት አብራት በምክትልነት ያገለገለችው ምትኬ አስማረ ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ተቃርበዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ