አርባምንጭ ከተማን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያገናኘው የ34ኛ ጨዋታ ሳምንት ቀዳሚው መርሐግብር ነጥብ በማጋራት ተጠናቋል።
አርባምንጭ ከተማ በ33ኛው ጨዋታ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡናን 1ለ0 ሲያሸንፉ ከተጠቀሙት ቋሚ አሰላለፍ አንድ ለውጥ ብቻ በማድረግ ኢድሪሱ ኦጎዶጆን በፋሪስ አላዊ ተክተው ሲገቡ ቅዱስ ጊዮርጊሶች በበኩላቸው ባሳለፍነው ጨዋታ ሳምንት ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ ይዘው ከገቡት ቋሚ ስብስብ የአራት ተጫዋቾች ለውጦችን አድርገው ሄኖክ ዩሐንስን በቶሎሣ ንጉሴ፣ አብርሃም ጌታቸውን በአፈወርቅ ኃይሉ፣ በረከት ወልዴን በአማኑኤል አረቦ፣ ፍፁም ጥላሁንን በቢኒያም ፍቅሩ ተክተው ገብተዋል።
የጨዋታ ሳምንቱ ቀዳሚ ጨዋታ ቀን ዘጠኝ ሰዓት ሲል አርባምንጭ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ አገናኝቷል። አዞዎቹ አሸንፈው ከወራጅ ስጋት ሙሉ ለሙሉ ለመውጣት እንዲሁም ፈረሰኞች ስጋት ባይኖራቸው ደረጃቸውን ለማሻሻል ወደ ሜዳ በገቡበት በአንደኛው አጋማሽ ፈረሰኞቹ በመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች ውስጥ በተደጋጋሚ የገቡ ሲሆን 8ኛው ደቂቃ ላይ ቢኒያም ፍቅሩ ከተከላካዮች መሐል የሰነጠቀለት ኳስ ዳግማዊ አርአያ አግኝቶ ከግብ ጠባቂው ፊት ለፊት ተገናኝቶ ሳይጠቀም የቀረበት ወርቃማው አጋጣሚ ይጠቀሳል። አዞዎቹም በአንፃራዊነት ኳስ ተቆጣጥረዝ በእርጋታ ወደ ፊች እየሄዱ የግብ እድል ለመፍጠር ጥረት ያድርጡ እንጂ ይሄ ነው ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ግልፅ የሆነ ሙከራ ማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል።
ተቀራራቢነት ያለው የጨዋታ እንቅስቃሴ በታየበት በመጀመሪያዎቹ ሀያ ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች ኳስ ተቆጣጥረው የበላይነት ለመውሰድ ብለውም በፈጣን ሽግግር ቶሎ ቶሎ ወደ ተጋጣሚዎቻቸው ግብ ክልል የደረሱበት የነበር ቢሆንም አጋጣሚዎችን ወደ ግብ ለመቀየር ጠንካራ ሙከራ አላስመለከቱንም። በመስመር በኩል እየገቡ ጥቃት ሲሰነዝሩ የነበሩት ፈረሰኞቹ 25ኛው ደቂቃ ላይ ከተከላካይ ጀርባ ተጥሎ ተጨራርፎ የተገኘውን ኳስ ዳግማዊ አርአያ ሳጥን ውስጥ ጠጠር ያለ ኳስ ወደ ግብ መጥቶ ኢላማውን ሳይጠብቅ ይቅር እንጂ ሌላኛውን አደገኛ ሙከራ አድርገዋል።
በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚዎቻቸው ግብ ክልል በመድረስ ረገድ ብልጫ የነበራቸው ፈረሰኞቹ ይዘው የሚገቡትን አጋጣሚዎች ወደ ግብነት ለመቀየር የሚያደርጉት ጥረት እየተቆራረጠባቸው ሲቸገሩ አስተውለናል። አዞዎቹም በበኩላቸው እንደመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ወደ ፊት መሄድ ያልቻሉ ሲሆን በመጠኑ መቀዛቀዝ ታይቶባቸዋል። 42ኛው ደቂቃ ላይ ከራሳቸው ሜዳ ፀጋዬ አበራ በረጅሙ የጣለውን ኳስ አህመድ ሁሴን ደርሶ ሳይጠበቅ ደካማ ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ያመከነው ወርቃማው አጋጣሚ አዞዎቹ የጨዋታውን ሂደት ቀይረው ወደ መልበሻ ክፍል እንዲገቡ ሊያስችላቸው የቀረበ እድል የነበረ ቢሆንም መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል።
በአጋማሹ ከፍተኛ ፉክክር ከፈጣን ሽግግሮች ጋር ታጅቦ ቢካሄድም ቡድኖቹ ጥራት ያላቸውን ሙከራዎች ማድረግ ፍፁም ተስኗቸው የጠራ ሙከራ ሳያስመለከትኑ እንዲሁም ግብ ሳያስቆጥሩ የመጀመሪያው አርባ አምስት ተጠናቆ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።
ጨዋታው በሁለተኛው አጋማሽ ሲመለስ አአረባምንጭ ከተማዎች የመጀመሪያ አጋማሽ አጨዋወት ቀይረው የገቡ ሲሆን በአንፃራዊነት የግብ አጋጣሚዎችን ፈጥረዋል። ከአጋጣሚዎችም መካከል 59ኛው ደቂቃ ላይ በረጅሙ የተጣለውን ኳሶ አህመድ ሁሴን ጨርፎ አሻግሮለት በፍቅር ግዛው አግኝቶ ደካማ ኳስ ወደ ግብ መጥቶ ባህሩ ነጋሽ በቀላሉ የተቆጣጠረባቸው የአዞዎቹ ጥሩ የማጥቃት እንቅስቃሴ ሲጠቀስ በተለየም 70ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው መሪሁን መስቀሌ ያደረገው ሙከሪ ተጠቃይ ነበር፤ ተጫዋቹ ከሳጥን ውጪ ርቀት ላይ ሆኖ አክርሮ የመታው ኳስ ግብ ጠባቂው እንዴትም ያግድበት እንጂ ጠንከራው እና አደገኛው ሌላኛው ሙከራ ነበር።
ፈረሰኞቹ በበኩላቸው በሀሉተኛው አጋማሽ በመልሶ ማጥቃት ወደ ፊት ሲሄዱ ያስተዋልን ቢሆንም እንደመጀመሪያው አጋማሽ በተደጋጋሚ ወደ ፊት የመሄድ ነገር ማሳየት አልቻሉም። ሆኖም ግን አልፈው አለፈው ሙከራዎችን ሲያደርጉ አስተውለናል፤ 67ኛው ደቂቃ ላይ ጳውሎስ ከንቲባ በመስመር በከል ሆኖ ያሻማውን ኳስ አማኑኤል አረቦ በግንባሩ ገጭቶ ያደረገው ሙከራ ለጥቂት ከግቡ አግዳሚ አናት ያለፈበት አጋጣሚ ፤ እንዲሁም 79ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው እራሱ ጳውሎስ ከንቲባ ተጨራርፎ የተገኘውን ኳስ ከሳጥን ውጭ ሆኖ ጠንከር ያለ ሙከራ አድርጎ ከግቡ ቋሚ ብረት ለትንሽ ርቆ ያለፈባቸው ሌላኛው ሙከራ ይጠቀሳል።
በሁለተኛው አጋማሽ ተሻሽለው የቀረቡት አርባምንጭ ከተማዎች ከአንደኛው አጋማሽ በአንፃራዊነት ወደ ፊት በመሄድ ረግድ ተወስዶባቸው የነበረዝ የጨዋታ ብልጫ ወስደው የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረጉ በሂደት ግብ ለማስቆጠር ወደ ሶስተኛው ሜዳ ክፍል ሲደርሱ አስተውለናል።
ጨዋታው በእንቅስቃሴ ረገድ ጥሩ ፉክክር የታየበት ቢሆንም ግልፅ ከሆኑ ግብ ማግባት ሙከራዎች ጋር ሳይታጀብ ወደ መጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ሲያመራ 85ኛው ደቂቃ ላይ ፈረሰኞቹ የጨዋታውን ውጤት ለመቀየር የቀረበ ሙከራ አድርገዋል። በተጠቀሰው ደቂቃ አላዛር ሳሙኤል ከሳጥን ውጭ ሆኖ ወደ ግብ ያሻገረውን ኳስ ግብ ጠባቂው ፋሪስ አግዶበት እራሱን ኳስ ወደ ግብ መጥቶ በድጋሚ ግብ ጠባቂው ያወጣባቸው አጋጣሚ ምናልባትም ለፈረሰኞቹ ሙሉ ሶስት ነጥብ ለማስገኘት የቀረበ አጋጣሚ ቢሆንም የፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ እድሉን እንዲጠቀሙ አላደረጋቸውም።
በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ፈረሰኞቹ በቁጥር በርከት ብለው በመግባት ጫና ሲያሳድሩ አዞዎቹ በአንፃራዊነት ወደ ኋላ አፈግፍገው ይዘው የሚገቡትን ኳስ ወደ ማምከን የገቡበትን ደቂቃዎች ሲያሳልፉ አስተውለናል። ሆኖም ግን ጨዋታው ግብ ሳይቆጠረብት ነጥብ በማጋራት ተጠናቋል።
ከጨዋታው በኋላ በተሰጡ አስተያየቶች አሰልጣኝ በረከት ደሙ ጎል እንዳይቆጠርብን ማድረግ የመጀመሪያ አላማቸው እንደነበር እና በዚህ አስቸጋሪ እና ውድ ወቅት ሲሉ በገለፁት በዚህ ወቅት አንድ ነጥብ ማግኘታችን በጣም መልካም ስለመሆኑ አንስተዋል በአንፃሩ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በበኩላቸው የመጨረሻ ሜዳ ክፍል ላይ ድክመት እንዳለባቸው አንስተው ጊዮርጊስ የሚለካው እያንዳንዱን ጨዋታ በማሸነፍ ስለሆነ ለማሸነፍ መግባታቸው ጫና እንዳሳደረባቸው ተናግረው ነፃ ሆነው እንዳልተጫወቱም ገልፀዋል።