ዋልያዎቹ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅታቸውን ለማጠናከር ከነበልባሎቹ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ሳኦ ቶሜና ፕሪንሲፔን በድምር ውጤት 4ለ0 አሸንፎ ለምድብ ድልድሉ የበቃው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ራሱን ለመፈተሽ ከማላዊ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ መሆኑን የማላዊ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።
የማላዊ አሰልጣኝ የሆኑት ካሊስቶ ፓሱዋ ከዋልያዎቹ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በተለይም የማጥቃት እንቅስቃሴያቸውን ለማሻሻል እንደሚረዳቸው ያላቸውን እምነት የገለፁ ሲሆን ጨዋታዎቹ የሚካሄዱበት ቀንም ይፋ ተደርጓል።
በዚህም መሠረት
የመጀመሪያው ጨዋታ – ግንቦት 29/2018
ሁለተኛው ጨዋታ – ሰኔ 2/2018
በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄዱ ይሆናል።
ኢትዮጵያና ማላዊ ካደረጓቸው ያለፉት ስምንት ጨዋታዎች መካከል ማላዊ 3 ጊዜ ፣ ኢትዮጵያ 1 ጊዜ ድል ሲያደርጉ ቀሪዎቹ 4 ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።
ሁለቱ ቡድኖች ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሲሆን ጨዋታው ያለምንም ግብ (0-0) መጠናቀቁ ይታወሳል።

