ፕሪምየር ሊግ ትኩረት | የፈረሰኞቹ የመለያ ስፓንሰሮች ጉዳይ

ፕሪምየር ሊግ ትኩረት | የፈረሰኞቹ የመለያ ስፓንሰሮች ጉዳይ

ሁለት የጨዋታ ሳምንታት ሁለት የተለያዩ የስፓንሰር አደራደሮችና ቀለም አጠቃቀም

ፈረሰኞቹ በአዲሱ የ2019 የውድድር ዘመን የሚጠቀሙባቸውን መለያዎች ከቀናት በፊት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል ታድያ ከእነዚሁ መለያዎች መካከል በመጀመሪያ የጨዋታ ሳምንት በሜዳቸውን የሚጠቀሙበትን ቢጫ መለያ ቡድኑ ከነጌሌ አርሲ ጋር ሲጫወት ጥቅም ላይ ማዋሉ አይዘነጋም ፤ በሁለተኛ ሳምንት በተጠባቂው የደርቢ ጨዋታ ላይ ግን ቡድኑ በተመሳሳይ የመጀመሪያ ተመራጭ መለያውን ቢጠበቀምም በመጀመሪያ ጨዋታ ከተጠቀሙት መለያ በግልፅ የሚስተዋሉ ልዮነቶች መኖራቸውን አስተውለናል።

ገና ከጅምሩ አዳዲሶቹ የፈረሰኞቹ መለያዎች ይፋ ከተደረጉበት ወቅት አንስቶ በተለይ በመለያው ደረት ላይ የሰፈረው ተቋም ሎጎ መጠንና ቀለም በደጋፊዎች ዘንድ ጥያቄ አስነስቶ የነበረ ሲሆን በመለያው የቀኝ ክፍል ላይ እንዲሁ ያለው የክለቡ አጋር ሎጎም መጠን እንዲሁ በጣም የገዘፈ ነው በሚል ሀሳቦች ሲሰነዘሩም እንዲሁ አድምጠናል።

ይህንንም ለማስተካከል በተለይም ከደረት ስፓንሰሩ ጋር ተያይዞ ለተነሱት ሀሳቦች ምላሽ ለመሰማራት ጠት በዚህ የጨዋታ ሳምንት ቡድኑ ባስተዋወቀው መለያ ደረት ላይ በሰማያዊ መደብ ላይ የነበረው የተቋሙ ቅይጥ ሎጎ (Hybrid Logo) በቃላት ብቻ (Word Marks Logo) ተቀይሮ በመለያው ደረት በነጭ ቀለም ሰፍፎ የተመለከትን ሲሆን ይህም ማሻሻያ በተለይ የክለቡ በሜዳው በሚጠቀመው ቢጫ መለያ ላይ ፍፁም ለማየት አስቸጋሪ እንደነበርም ለማስተዋል ችለናል ፤ ምንም እንኳን ይህ ማሻሻያ በሁለተኛ እና ሶስተኛ አማራጭ መለያዎች(ቀይና ጥቁሩ) ላይ ለዕይታ(Visibility) ባያስቸግሩም ክለቡ በዓመቱ በአመዛኙ በተደጋጋሚ በሚጠቀመው ቢጫው መለያ ላይ ግን እምብዛም ስሜት የሚሰጥ ሆኖ አላገኘነውም።

ዓለም ላይ የስፓንሰር አድራጊ ተቋማት ሎጎዎች በመለያዎች ላይ የሚሰፍሩበት መንገድ ላይ እያንዳንዱ ጉዳይ ማለትም (ስፍራ ፣ መጠን ፣ ቀለምና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች የድርጅቱን የዕይታ ተደራሽነት እንዲሁም ከመለያ ውበት ጋር በቀጥታ ዝምድና ያለው እንደመሆኑ በዝርዝር የሚጤን ሲሆን ለምሳሌ በቅርቡ የቼልሲ የመለያ የደረት ላይ ስፓንሰር ለመሆን የተስማማው ግዙፉ የአሜሪካ ተቋም “Circle” “USDC” የተሰኘው ምርቱ ምንም እንኳን ምርቱ በተናጥል እንዲሁም ኩባንያው በራሱ የራሳቸው የሆነ ተቋማዊ ቀለም (Brand Colour) ቢኖራቸውም ከቼልሲ የዘንድሮ የመለያ ዲዛይን የቀለም ስብጥር ጋር እንዲጣጣም በሚል ከተቋማዊ ቀለማቸው ውጭ በቼልሲ መለያ ላይ ከተካተተው ቢጫ ቀለም ጋር እንዲጣጣም በሚል በመለያው ላይ በቢጫ ቀለም ታትሞ መመልከት ችለናል።

ለአብነት ይህን የቅርብ ጊዜ ጉዳይ አነሳን እንጂ (Etihad Airways ፣ Standard Charterd ፣ AIA፣ Snapdragon) የተሰኙትና በታላላቅ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ደረት ላይ የምንመለከታቸው ስፓንሰሮች ከተቋማዊ ቀለማቸው ውጭ ከክለቦቹ መለያ ቀለምና ዲዛይን ጋር እንዲናበብ በሚል የቀለም ለውጥ ተደርጎባቸው የሰፈሩ መሆናቸውን ልብ ይሏል።

ከደረት ስፓንሰር ባለፈ ቡድኑ በዚህ ሳምንት የተጠቀመበት መለያ በመጀመሪያ ሳምንት በተቀመው መለያ ላይ በእጀታው ላይ የነበረ አንድ ስፓንሰር ከመለያው ላይ እንዲነሳ የተደረገ ሲሆን ከመለያው ጀርባና እጀታ ላይ የነበሩ ስፓንሰሮችም እንዲሁ ቦታቸውን ተቀያይረው ተመልክተናል።

መሰል ለውጦች በውድድር ዘመን መሀል የተለመዱ ባይሆንም አስቀድመው ማለቅ የሚገባቸው ጉዳዮች በወቅቱ ባለማለቃቸውና ተራማጅ ያልሆኑ እሳቤዎች በእግር ኳሳችን መንገሳቸው በምክንያትነት ቢጠቀስም መለያውን የሚገዙ ደጋፊዎች ላይ ከሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ አንፃር በፍጥነት መፍትሄን ይሻል።