ኢትዮ ኤሌክትሪክ የመጀመሪያ ድሉን ሲያሳካ በርበሬዎቹና ዐፄዎቹ ነጥብ ተጋሩ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ የመጀመሪያ ድሉን ሲያሳካ በርበሬዎቹና ዐፄዎቹ ነጥብ ተጋሩ

በአብዩ አረጋሽ

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሸገር ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ሀላባ ከተማና ፋሲል ከነማ 1ለ1 ተለያይተዋል

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ሸገር ከተማ

የዕለቱ ቀዳሚ የነበረው ይህ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪኮች መሪ ለመሆን የፈጀባቸው ደቂቃ ሦስት ብቻ ነበር። አዲስ ፈራሚው ካሌብ ሴትፍሜልቪን ጨዋታው በተጀመረ በ3ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብም ቡድኑን መሪ ያደረገች ግብ ነች።

በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ ብቃት ያሳየው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሁለተኛው አጋማሽም የሸገር ከተማን ጫና ተቋቁሞ የአንድ ግብ መሪነቱን እስከ መጨረሻው ደቂቃ በማስጠበቅ ወሳኝ ሦስት ነጥቦችን ወስዶ የውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል።

ሀላባ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

10:00 ሰዓት በሀላባ ስታድየም በተደረገው ጨዋታ በበርካታ የግብ ሙከራዎች ታጅቦ የተካሄደና አዝናኝ ፉክክር የተደረገበት ነበር። ሀላባ ከተማ በ12ኛው ደቂቃ ላይ ካሌብ አማንክዋህ ከቆመ ኳስ ተሻምቶ በግምባር ባስቆጠረው ግብ መሪነቱን ይዞ አጋማሹን አጠናቋል።

ፋሲል ከነማ ከዕረፍት መልስ በ49ኛው ደቂቃ ላይ አዲስ ፈራሚው ሮማሪክ ዲንሆ ሌላው አዲስ የቡድኑ አዲስ ፈራሚ ጄሮም ኦዴ አሻምቶት ታምራት ኢያሱ በግምባሩ ገጭቶ ከመታው በኋላ ግብ ጠባቂው የመለሰውን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ ዐፄዎቹን አቻ ማድረግ ችሏል። በቀሪው የጨዋታ ክፍለ ጊዜም ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠር ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ በመጋራት ጨዋታቸውን ፈፅመዋል።