ሉሲዎቹ ከሜዳቸው ውጪ እጅግ ወሳኝ ድል ተቀዳጅተዋል

ሉሲዎቹ ከሜዳቸው ውጪ እጅግ ወሳኝ ድል ተቀዳጅተዋል

በዐቢዩ አረጋሽ

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ2028 ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ሩዋንዳን ኪጋሊ ላይ ገጥሞ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

መጠነኛ ፉክክር በተደረገበት የመጀመርያ አጋማሽ በሩዋንዳ በኩል ለግብ የቀረበ ሙከራ ያልተመለከትን ሲሆን በኢትዮጵያ በኩል 34ኛ ደቂቃ ላይ ግብ ጠባቂዋ ታሪኳ በርገና ኳስ ለማዳን ጥረት ስታደረግ ከሩዋንዳ ተጫዋች ጋር በተፈጠረው ግጭት ከሜዳ ተቀይራ ስትወጣ እሷን በመተካት ቤተልሔም ዮሐንስ ገብታለች  ።

መደበኛው 45 ደቂቃ ተጠናቆ በጭማሪው 7 ደቂቃ ውስጥ  45+1ኛው ደቂቃ ላይ ሴናፍ ዋቁማ ለምሕረት አየለ በቀኝ በኩል የሰጠቻትን ኳስ ምሕረት አየለ በቀኝ በኩል ወደ ፊት ገፍታ በሌላኛው አቅጣጫ ኳስን ወደ ግብነት ለመቀየር ምቹ ቦታ ላይ ለነበረችው ንግሥት በቀለ መሬት ለመሬት ኳሱን ስታሻግረው የሩዋንዳዋ ኡዛዬሴንጋ ሊድያ ኳሱን የራሷ ግብ ላይ አስቆጥራው ኢትዮጵያ 1-0 መሪ መሆን ችላ የመጀመሪያው አጋማሽም በዚሁ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል።

በሁለተኛው አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች በኩል በተመሳሳይ የተመጣጠነ ፉክክር የተመለከትን ቢሆንም ለግብ የቀረበ ሙከራ እምብዛም ሳንመለከት ጨዋታው 1ለ0 ተጠናቋል።

* መልሱ ጨዋታ ጥቅምት 3/2019 ዓ/ም በድሬዳዋ ይደረጋል።