በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት በተካሄደው የሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 2-1 አሸንፏል።

በዐቢዩ አረጋሽ
የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ግብ ቢጠናቀቅም፣ በ57ኛው ደቂቃ በፍቃዱ ዓለማየሁ እና በ74ኛው ደቂቃ ኦካይ ጁል ለኢትዮጵያ ቡና ግቦችን አስቆጥረዋል። በ82ኛው ደቂቃ አማኑኤል ኤርቦ ለቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ግብ ቢያስቆጥርም ቡድኑን ከሽንፈት ማዳን አልቻለም።

በጨዋታው የተጨማሪ ደቂቃዎች በረከት ወልደዮሐንስ በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲወገድ፣ በፍቃዱ ዓለማየሁ እና ያሬድ የማነም በፈጠሩት ሰጣገባ ሁለቱም በቀጥታ በቀይ ካርድ ተሰናብተዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ ቡና የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድልና ሦስት ነጥብ ሲያሳካ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንድ ነጥቡ ቀጥሏል።
ሀዋሳ ከተማ 1-1 ከኢትዮጵያ መድን
በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረጉት ጨዋታ 1–1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

በ23ኛው ደቂቃ አልፍሬድ ኩሩንዚዛ ለኢትዮጵያ መድን ግብ ሲያስቆጥር፣ በ62ኛው ደቂቃ ጌታነህ ከበደ በፍጹም ቅጣት ምት ሀዋሳ ከተማን አቻ አድርጓል።

ጨዋታው በቀይ ካርዶች የታጀበ ሲሆን፣ የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ አዲቢዬ ማርሴል እና የኢትዮጵያ መድኑ ዋንጫ ቱት በቀጥታ ቀይ ከሜዳ ተሰናብተዋል።
በመጨረሻም ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ ተጋርተው የሊጉን ጨዋታ አጠናቀዋል።

