ፋሲል ከነማ አማኑኤል ዮሐንስን ዝውውር አጠናቋል

አማኑኤል ዮሐንስ ዐፄዎቹን የተቀላቀለ አራተኛው ተጫዋች ሆኗል።

ከወጣት ቡድን አድጎ በኢትዮጵያ ቡና ዘለግ ያለ ቆይታን ያደረገው ይህ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ከቀናት በፊት ውሉ በክለቡ በመጠናቀቁ ምክንያት በኢትዮጵያ ቡና ለመቀጠል ቅድመ ስምምነትን የፈፀመ ቢሆንም በአንዳንድ ጥቅማጥቅሞች መስማማት ባለመቻሉ ወደ ጃኖ ለባሾቹ ቤት አምርቶ ቅድመ ኮንትራት መፈራረም ችሏል፡፡

ክለቡ አራት ተጫዋቾች ከማስፈረሙ በተጨማሪ የስድስት ተጫዋቾችን ውል ያራዘመ ሲሆን በቀጣይ የአምሳሉ ጥላሁንን ውል ለማደስ ንግግር ላይ እንደሆነ ታውቋል ፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ