ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ሀዋሳ ከተማ ሦስት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሦስት ነባሮችን ውል አደሰ

በቅርቡ አዲስ አሰልጣኝ የሾሙት ሀዋሳ ከተማዎች የሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ሲያጠናቅቁ የነባሮቹነም ውል አራዝመዋል፡፡

ከ2005 የፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎ አንስቶ በአሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ሲመሩ የነበሩት ሀዋሳ ከተማዎች በቅርቡ አሰልጣኝ መልካሙ ታፈረን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርገው መቅጠራቸው ይታወሳል፡፡ በሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ጠንካራ ተፎካካሪ ከሆኑ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ክለቡ ለዘንድሮው የውድድር ዘመን አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም ሲጀምር መሐሪ በቀለ፣ ዮዲት መኮንን (ፎቶ-ግራ) እና ፀሀይ ጁላ አዳዲስ ፈራሚ ተጫዋቾ ሆነዋል፡፡

በሀዋሳ ከተማ የክለብ ህይወቷን የጀመረችው አጥቂዋ መሐሪ በቀለ ክለቡን ከለቀቀች በኃላ ለሲዳማ ቡና፣ ጌዲኦ ዲላ እንዲሁም የተሰረዘውን የውድድር ዓመት በአቃቂ ቃሊቲ በመጫወት አሳልፋ ወደ ቀድሞ ክለቧ በሁለት ዓመት ውል ተመልሳለች፡፡ ሌላኛዋ ፈራሚ በመከላከያ ጥሩ የውድድር ጊዜያትን ስታሳልፍ የነበረችው አማካይዋ ፀሐይ ጁላ ስትሆን ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ የተገኘችውና በአዳማ ከተማ ሁለት ዓመታት የተጫወተችው የተከላካይ አማካይዋ ዮዲት መኮንን ሌሎች ፈራሚዎች ናቸው።

ክለቡ በርካታ ተጫዋቾች ውል ያላቸው ቢሆንም ሦስት ውላቸው የተጠናቀቁ ተጫዋቾችን ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል፡፡ በመሐል ተከላካይነት ለክለቡ ወሳኝ መሆኗን ያስመሰከረችው ቅድስት ዘለቀ (ፎቶ-ግራ)፣ የግራ መስመር ተከላካይዋ ፀሐይ ኢፋሞ እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋቿ በረከት ጴጥሮስም ለተጨማሪ ዓመታት ውል አራዝመዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!