ከፍተኛ ሊግ | ፌዴራል ፖሊስ የቀድሞ ኮከቡን በአሰልጣኝኘት ሲሾም አንድ ተጫዋች አስፈርሟል

የከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ክለብ ፌዴራል ፖሊስ የቀድሞ ታሪካዊ ተጫዋቹን በዋና አሰልጣኝነት ሲሾም አዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን አስፈርሟል።

በክለቡ ከግማሽ ክፍለ ዘመን የተሻገረ ታሪክ ድንቅ ከሚባሉ ተጫዋቾች አንዱ የነበረውና በቀድሞ አጠራሩ ኦሜድላ ከ 15 ዓመት በላይ የተጫወተው ተስፋዬ ፈጠነ ክለቡን ወደ ቀድሞ ዝናው የመመለስ ኃላፊነትን በአንድ ዓመት ውል የተረከበ ሲሆን ሌላው ለክለቡ ተጫውቶ ያሳለፈው ደሳለኝ ጁማ በረዳትነት የሚሰራ ይሆናል።

ከሌሎች ክለቦች ተጫዋቾችን ማዘዋወር በመቀነስ በሒደት ከፖሊስ ሠራዊቱ ተጫዋቾች በመመልመል ቡድኑን ለማወቀር የወሰነው ክለቡ ከጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን የተገኘው ተከላካዩ አቤል አየለን ለአንድ ዓመት ያስፈረመ ሲሆን ግብ ጠባቂው እስራኤል አለ እንዲሁም አጥቂው ብሩክ ብርሃኑ ደግሞ ውል ያራዘሙ ተጫዋቾች ሆነዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ