የወቅቱ ድንቅ ተጫዋች ልምምድ አቋርጦ ወጣ

የኢትዮጵያ ቡናው ኮከብ ልምምድ እየሰራ ባለበት ወቅት በገጠመው ጉዳት ልምምድ አቋርጦ ወጥቷል።

በቀጣይ ወር ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣርያ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት የመጀመርያ ልምምዱን ሲኤምሲ በሚገኘው ንግድ ባንክ ሜዳ እያደረገ በሚገኝበት ሰዓት የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ አቡበከር ናስት ቀኝ እጁ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ልምምድ ማቋረጡን መመልከት ችለናል። የጉዳቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ለማረጋገጥ ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ቢሆንም ከጅማው የፕሪምየር ሊግ ውድድር ጀምሮ የነበረ እና ለክፉ የማይሰጥ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

አቡበከር ናስር በዘንድሮ ዓመት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በሁሉም ረገድ ደምቆ የሚገኝ ሲሆን የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱንም እየመራ ይገኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ