ድሬዳዋ ከተማ የግብ ጠባቂውን ውል አራዘመ

ግብ ጠባቂው ፍሬው ጌታሁን በድሬዳዋ ከተማ ውሉን አራዝሟል።

የአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን ውል ካደሰ በኃላ ፊቱን ወደ ተጫዋች ዝውውር በማዞር ጋዲሳ መብራቴ እና እንየው ካሣሁንን ያስፈረመው ድሬዳዋ የወሳኝ ግብ ጠባቂው ፍሬው ጌታሁንን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል፡፡ የቀድሞው የአርሲ ነገሌ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዲስ አበባ ከተማ ግብ ጠባቂ በድሬዳዋ ከተማ ከ2012 ጀምሮ መጫወት የጀመረ ሲሆን ዘንድሮ ባሳየው መልካም የውድድር ዓመትን ታሳቢ በማድረግ በከፍተኛ የደመወዝ ማሻሻያ ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ዛሬ ውሉን አድሷል፡፡