ሴካፋ 2021| የዋልያዎቹ አስላለፍ ታውቋል

ከሁለት ሰዓታት በኋላ የኤርትራ አቻውን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ አሰላለፍ ታውቋል።

41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው ዋንጫ ውድድር ከሁለት ሰዓታት በኋላ ይጀምራል። በውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታም የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ይሆናል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ውበቱ አባተ በጨዋታው የሚጠቀሙት የመጀመርያ አሰላለፍም ታውቋል።

በዚህም የግብ ዘቡ ፅዮን መርዕድ ከግብ ብረቶቹ መካከል ሲቆም ኃይሌ ገብረትንሳኤ፣ መናፍ ዐወል፣ ሠለሞን ወዴሳ እና ረመዳን የሱፍ የቡድኑ አራት ተከላካዮች ሆነዋል። መሐል ሜዳ ላይ ሀብታሙ ተከስተ፣ አብዱልሃፊዝ ቶፊቅ እና ዊልያን ሠለሞን ተጣምረዋል። የቡድኑን የፊት መስመር ደግሞ ቸርነት ጉግሳ፣ ሙኧዲን ሙሳ እና አቡበከር ናስር እንደሚመሩት ተረጋግጧል።