ሎዛ አበራ የሉሲዎቹን ስብስብ ልትቀላቀል ነው

ሎዛ አበራ የሉሲዎቹን ስብስብ ልትቀላቀል ነው

ለአሜሪካው ዲሲ ፓወር የምትጫወተው አጥቂዋ ለሉሲዎቹ የመልስ ጨዋታ ወደ ኢትዮጵያ መጥታለች።

ለ2028 የሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ የሴቶች እግርኳስ ውድድር ለማለፍ በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ወደ ኪጋሊ ተጉዞ ሩዋንዳ ላይ የ1ለ0 እጅግ ወሳኝ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል።

በቡድኑ የዝግጅት ጊዜያት ጥሪ ቀርቦላቸው ከነበሩት በውጪ ሀገር ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ቡድኑን ሳትቀላቀል ቀርታ የነበረችው ሎዛ አበራ ለመልሱ ጨዋታ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቷ ታውቋል።

በአዲስአበባ ደብረዳሞ ሆቴል ማሪፊያዋን ያደረገችው አጥቂዋ ብሔራዊ ቡድን አዲስ አበባ ገብቶ ወደ ድሬዳዋ ጉዞ ሲጀምር አንድ ላይ ወደ ድሬዳዋ ከተማ እንደምታቀና ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።