የወልዋሎ ጨዋታ የሰዓት ለውጥ ተደረገበት።

ወልዋሎ ዓ/ዩ ወደ ሊብያ አምርቶ ከአል አህሊ ትሪፖሊ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ከቀኑ 10:00 ሰዓት እንዲካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለት እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ዛሬ በተካሄደው የቅድመ ጨዋታ ውይይት ቀደም ብለው ሁለቱም ቡድኖች ጨዋታው ከምሽቱ 2:00 ሰዓት እንዲካሄድ ከስምምነት እንደደረሱ ታውቋል።
ቀደም ብለን እንደገለፅነው ወልዋሎ ዛሬ ረፋድ የመጨረሻ ልምምዱ የሰራ ሲሆን ተጋጣሚው አል አህሊ ትሪፖሊ ደግሞ ዛሬ ምሽት የመጨረሻ ልምምዱን እንደሚሰራ ታውቋል። በወልዋሎ በኩል ከአማካዩ ማማዱ ሴክ ውጭ ሁሉም ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም ታውቋል።

