የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሰበታ ከተማ ጨዋታ ነገ ይካሄድ ይሆን?

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ሳምንት የቀን ለውጥ ተደርጎበት ነገ ሊካሄድ የታሰበው የቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሰበታ ከተማ ሊያደርጉት የነበረው መርሐ ግብር እክል አጋጥሞታል።

14ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል ምክንያት ቅዳሜ እና እሁድ ሊደረጉ የነበሩ ሁለቱ ጨዋታዎች የቀን ለውጥ ተደርጎባቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሰበታ ከተማ ነገ (ማክሰኞ ኅዳር 30 ቀን በ11:00) እንዲሁም ረቡዕ ታህሳስ 1 ቀን በ11:00 የኢትዮጵያ ቡና እና ጅማ አባ ጅፋር በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲጫወቱ መወሰኑ ይታወቃል።

ሆኖም ነገ የሚደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የሰበታ ከተማ ጨዋታ የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል። ምክንያቱ ደግሞ በካታንጋ አካባቢ በአጠና የተሰራው ርብራብ ከበዓሉ መጠናቀቅ በኋላ ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ሙሉ ለሙሉ አለመነሳቱ ነው። የተሰራው ርብራብ እስካሁን አለመፍረሱ ያሳሰበው የሊጉ ዐቢይ ኮሚቴም ለሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት እንዲነሳ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ርብራቡን ለመስራት ከወሰደው ጊዜ አንፃር ነገ ከማለዳው ጀምሮ የማፍረስ ሥራ በፍጥነት ካልተሰራ በቀር ቦታውን ለተመልካች ዝግጁ ለማድረግ አስቸጋሪ እንደሆነም ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ