ባህር ዳር ከተማ አራተኛ ተጫዋች አስፈርሟል

በ2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጠናክሮ ለመቅረብ ዝውውሮች ላይ ጠንክሮ እየሰራ የሚገኘው ባህር ዳር ከተማ አራተኛ ተጫዋች አስፈርሟል።

አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን ከቀጠሩ በኋላ ፉዐድ ፈረጃ፣ መሳይ አገኘሁ እና ተመስገን ደረሰን የግላቸው ያደረጉት ባህር ዳር ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊት በሁለት ዓመት ውል አለልኝ አዘነን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

በአርባምንጭ ከተማ የእግር ኳስ ህይወቱን በ2008 የጀመረው እና በክለቡም እስከ 2011 ድረስ የቆየው ቁመተ መለሎው ተጫዋች ከ2012 እስከ ተጠናቀቀው የውድድር ድረስ ደግሞ በሀዋሳ መለያ በመጫወት አሳልፏል፡፡ በ2012 በቅጣት ለአንድ ዓመት ከሜዳ ርቆ በ2013 አጋማሽ ወደ ሜዳ የተመለሰው አማካዩ ወደ ጣና ሞገዶቹ ቤት በሁለት ዓመት ውል አምርቷል፡፡