የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ዙር የምድብ ሀ ውድድር የሚደረግበት ከተማ ለውጥ ተደርጎበታል

መጋቢት 10 በሚጀምረው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የምድብ ሀ ጨዋታዎች የሚደረጉበት ስፍራ ለውጥ ተደርጎበታል።

\"\"

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያወዳድረው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የመጀመሪያው ዙር ከሳምንታት በፊት መጠናቀቁ ይታወሳል። የሁለተኛ ዙር ውድድር ደግሞ በሆሳዕና፣ ባቱ እና ሐዋሳ ከተሞች ከመጋቢት 10 ጀምሮ እንደሚደረጉ ይፋ ሆኖ ነበር።

አሁን የውድድሩ የበላይ አካል የሆነው ፌዴሬሽኑ የምድብ ሀ ውድድርን ወደተሻለ ሜዳ ማዘዋወር በማስፈለጉ በማለት ሆሳዕና ላይ ሊደረግ የነበረውን ውድድር ወደ አሰላ ከተማ ማዘዋወሩን አሳውቋል። የምድብ ለ እና ሐ የውድድሮች ስፍራዎች ግን አስቀድሞ በተያዘላቸው ከተማ እንደሚካሄዱም ተገልጿል።

\"\"