ጌቱ ኃይለማርያም ወደ ቢጫዋቹ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

በ16 ነጥብ 19ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቁት ወልዋሎዎች የመስመር ተከላካዩ ጌቱ ኃይለማርያምን ለማስፈርም ከስምምነት ደርሰዋል። ከዚህ ቀደም በሰበታ ከተማ፣ ወልቂጤ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ የነበረው ተከላካዩ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ወልዋሎን ለመቀላቀል ተስማምቶ ዝውውሩ በአንዳንድ ጉዳዮች ከከሸፈ በኋላ አሁን ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በኋላ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመልሷል። ቢጫዎቹ ቀደም ብለው በክዋራ ዩናይትድ፣ ስፖርቲንግ ሌጎስ፣ ሹቲንግ ስታርስ እና ኬንያ ፖሊስ መጫወት የቻለውን ናይጄርያዊ አጥቂ ሳሙኤል አያንሪንዴ ወደ ስብስባቸው መቀላቀላቸውንም ይታወሳል።

