፡፡አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ስለ ወቅታዊ የብሄራዊ ቡድኑ ሁኔታ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ ከንግግሮቹ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
-“በዛምቢያው ጨዋታ ያየናቸው ክፍተቶችን ሙሉ ለሙሉ ሸፍነናል ማለት አንችልም፡፡ ነገር ግን በስብስቡ ውስጥ ከግማሽ በላዩ ስለሚቀየር ክፍተታችንን በተሸለ ሁኔታ እንደፍናለን ብለን እናስባለን፡፡”
-“በማጣርያ ጨዋታዎቹ ጉዞ ላይ በእያንዳንዱ ጨዋታ የራሳችንን አድል በራሳችን ለመወሰንና በሌሎች ቡድኖች ላይ ሳንንጠለጠል ማጣርያውን በብቃት ለመወጣት እንጥራለን፡፡”
-“ማንኛውም ጨዋታ ጫና አለው፡፡ በሁሉም ደረጃ ማንኛውም ውድድር ጫና አለው፡፡ የህንን ጫና የመቋቋምና ውጤት የማስመዝገብ ኃላፊነት አለብን፡፡ ለዚህ ጫናው የሚያስፈራን ሳይሆን ጤናማ ነው፡፡”
-“የጨዋታ ትንሽ የለውም፡፡ እነርሱም እኛም 3 ነጥብ ለማግኘት ነው የምንጫወተው፡፡ በምንም መንገድ ለሌሶቶ ዝቅተኛ ግምት መስጠት አንችልም፡፡”
-“ከአዲስ አበባ እዚህ የመጣነው የአዲስ አበባ የአየር ንብረት አስተማማኝ ስላልሆነ ነው፡፡ እዚህ በአየሩ ምክንያት ልምምድ አምልጦን አያውቅም፡፡ሜዳውም ለመጫወት ምቹ ነው፡፡ ተጫዋቾቹ ሲቀላለዱ እንደሰማሁትም ‹‹ በዚህ ሜዳ ኳስ ማቀበል የማይችል ተጫዋች ኳስ አይችልም፡፡
-“ስለ ሌሶቶ የሚወራው ነገር ሁሉ እኛን ለማዘናጋት ነው፡፡ እንደውም ከኛ በተሸለ በበቂ ሁኔታ ተዘጋጅተዋል፡፡ ከ1 ወር በላይ የተዘጋጁ ሲሆን ኮሳፋ ውድድር ላይ የተጠቀሙበትን ቡድን ነው ይዘው የሚመጡት፡፡”
-“አላማችን አሸንፎ መውጣት ነው፡፡ በሜዳችን የምናደርገው ጨዋታ ሲሆን የመጀመርያ ጨዋታችን እንደመሆኑም ማሸነፍ አለብን፡፡”