‹‹ ዝናቡ በሚገባ ጠቅሞናል ›› በኃይሉ አሰፋ

የብሄራዊ ቡድኑ 2ኛ አምበል በኃይሉ አሰፋ ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ በሰጠው ድህረ ጨዋታ አስተያየት ስለ በጨዋታው ስለተከሰቱ ጉዳዮች ማብራርያ ሰጥቷል፡፡

‹‹ ዝናቡ ጠቅሞናል ››

‹‹ ዝናብ መዝነቡ የፈጠረብን ችግር የለም ፡፡ እንደውም ሁለት ግቦች እንድናስቆጥር እገዛ አድርጎልናል፡፡ ሜዳው ጥራቱን የጠበቀ በመሆኑ ኳሱን እንደፈለግነው ከማንሸራሸርም ያገደን ነገር አልነበረም፡፡ ዝናቡ በሚገባ ጠቅሞናል፡፡ ለጋቶች ግብም የራሱን የሆነ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ምክንያቱም ኳሷ ላይ ፍጥነት ጨምሮባታል፡፡ ›› ብሏል፡፡

ሌሶቶ . . .

‹‹ በሚድያዎች እንደሚነገረው ሌሴቶ ቀላል ቡድን አይደለችም፡፡ በቀላሉ በርካታ ግቦች ማስቆጠር እንደምንችል ተገምቶ ነበር፡፡ እንኳን የሌሶቶ ብሄራዊ ቡድን ላይ የሰፈር ቡድን ላይ 9 ግብ በቀላሉ ልናስቆጥር አንችልም፡፡ ››

ጫና . . .

ቁጥሩ ከፍተኛ ደጋፊ ስለነበር ግፊቱ ከባድ ነበር፡፡ በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ከተሳተፍን በኋላ የ2015ቱ ስላለፈን በ2017 በድጋሚ አፍሪካ ዋንጫው ላይ የመሳተፍ ጫና ውስጥ ገብተናል፡፡ በዚህም ምክንያት በመጀመርያው አጋማሽ እንደልብ መንሳቀስ አልቻልም ነበር፡፡ ››

‹‹ ህዝቡ ትልቅ ኃይል ሆኖን ነበር ››

‹‹ በጨዋታው መስራት ያለብንን ነገር አሳክተናል ብዬ አስባለሁ፡፡ የመስመር እንቅስቃሴያቸውን ዘግተነው ነበር፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ለውጥ ፈጥረን ስህተቶቻችንን በማረም ግቦች ማስቆጠር ችለናል፡፡ ህዝቡ ትልቅ ኃይል ሆኖን ነበር፡፡››

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *