የሃሳኒያ አጋዲር እና ጅማ አባ ጅፋርን የመልስ ጨዋታ አልጀሪያዊያን ይመሩታል

አልጀሪያዊው ኢንተርናሽናል አርቢትር ናቢል ቡካልፋ በሞሮኮው ሃሳኒያ ኢዩ. ኤስ አጋዲርና በኢትዮጵያው ጅማ አባ ጅፋር መካከል የሚደረገውን የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡ 

ቅዳሜ ጥር 11 ምሽት በሞሮኮ አጋዲር ከተማ አድራር ስታዲየም የሚደረገውን የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ ከመሃል ዳኛው ናቢል በተጨማሪ አልጀሪያውያኑ ሞክራን ጉራሪና አቤስ አክራም ዜርሁኒ በመስመር ዳኝነት ይመሩታል፡፡ 

የዚሁ ማጣሪያ መጀመሪያ ጨዋታ ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተደርጎ ሃሳኒያ አጋዲር ዞሒር ቻውች ባስቆጠረው ብቸኛ ጎል 1-0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *