የድሬደዋ ከተማ እና የአብዱራህማን ሙባረክ ጉዳይ ውሳኔ አግኝቷል

ድሬደዋ ከተማ በአብዱራህማን ሙባረክ ጉዳይ ዙርያ የዲሲፕሊን ውሳኔ ተላልፎበታል።

ባሳለፍነው ዓመት ድሬደዋ ከተማን የተቀላቀለው አብዱራህማን ሙባረክ ቀሪ አንድ አመት ኮንትራት እየቀረው ከክለቡ ጋር እንዲለያይ መደረጉን ተከትሎ ተጫዋቹ ቅሬታውን ወደ ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፒሊን ኮሚቴ ይዞ መሄዱ ይታወሳል።

ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የዲሲፒሊን ኮሚቴ ከሁለት ቀን በፊት በወሰነው ውሳኔ መሠረት ተጫዋች አብዱራህማን ሙባረክ ያልተከፈለው የሦስት ወር ደሞዝ እንዲከፈለው፣ መልቀቂያ እንዲሰጠው እና ተጫዋቹ በክርክር ላይ የነበረ መሆኑ ታውቆ በዲሲፒሊን ኮሚቴ መመርያ አንቀፅ 89(ሀ) መሠረት በክለብ የመመዝገብ መብቱ ተጠብቆ በፈለገው ክለብ ገብቶ እንዲጫወት ትዕዛዝ ተሰጥቷል።