የአስቻለው ግርማ ማረፊያ ታውቋል

ከቀናት በፊት ከሰበታ ከተማ ጋር በስምምነት የተለያየው አስቻለው ግርማ ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቀለ፡፡

ቀስ በቀስ በሊጉ ያስፈረሟቸውን ተጫዋቾች ቁጥር በርከት ያደረጉት ድሬዳዋ ከተማዎች አሁንም አዲስ ተጫዋቾች ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል፡፡ አስቻለው ግርማ ደግሞ በአንድ አመት ውል የክለቡ አዲሱ ፈራሚ ሆኗል፡፡ ከሱሉልታ ከተማ ከተገኘ በኃላ በኢትዮጵያ ቡና ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ጅማ አባጅፋር መጫወት የቻለው የመስመር አጥቂው በተሰረዘው የውድድር ዓመት ለሰበታ ከተማ ለሁለት ዓመት ለመጫወት ፈርሞ የነበረ ቢሆንም አንድ ዓመት የውል ጊዜ እየቀረው ከቀናቶች በፊት ከሰበታ ጋር በመለያየት ወደ ምስራቁ ክለብ ቀጣይ ማረፊያውን አድርጓል፡፡

በመጀመሪያው የሰበታ ጨዋታ በመስመር ማጥቃት ችግር የነበረበትን ክለብ የተጫዋቹ መምጣት ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ