ከፍተኛ ሊግ | ጋሞ ጨንቻ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

በቅርቡ አዲስ አሰልጣኝ የቀጠረው ጋሞ ጨንቻ ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ የሚወዳደረው እና በቅርቡም ግዛቸው ጌታቸውን በዋና አሰልጣኝነት የሾመው ጋሞ ጨንቻ ለ2015 የውድድር ዘመን አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ራሱን እያጠናከረ ይገኛል፡፡ ክለቡም ከተለያዩ ክለቦች ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሞ ወደ ዝግጅት ገብቷል፡፡

በዚህም ክለቡ በድሉ ሠለሞን (አጥቂ) ከጎፋ ባራንቼ ፣ ንጉሴ ሙሉጌታ (ግብ ጠባቂ) እና ደሳለኝ አሎን (አማካይ) ከሀላባ ከተማ ፣ ግርማ ዮሐንስ (አማካይ) ከጅማ አባጅፋር ፣ ሠለሞን ጌታቸው (አጥቂ) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ንጋቱ ፀጋዬ (ተከላካይ) ከቤንች ማጂ ቡና ፣ ፊናሰ ተመስገን (አማካይ) ከሶዶ ከተማ እና ዘላለም ኢያሱ (አጥቂ) ከቦዲቲ ከተማ ናቸው፡፡

ከአዲስ ፈራሚዎች በተጨማሪ ከታዳጊ ቡድኑም አምስት ተጫዋቾችን ማሳደጉን ለድረ-ገፃችን ክለቡ የላከው መረጃ ይጠቁማል፡፡