ሲዳማ ቡና ግዙፉን አጥቂ በይፋ አስፈርሟል

ሲዳማ ቡናዎች ከዚህ ቀደም ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል የተስማሙት አጥቂ በይፋ ማስፈረማቸው ተረጋግጧል።

በአሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ የሚመሩት ሲዳማ ቡናዎች የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል ካደሱ በኋላ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው በመቀላቀል ለ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እየተዘጋጁ ይገኛሉ። ከወራት በፊትም ለማስፈረም ተስማምተውት የነበረው ግዙፉ ማሊያዊው አጥቂ ማማዱ ሲዲቤ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ በይፋ ቡድኑን እንዲቀላቀል ማድረጋቸው ተረጋግጧል።

2011 ላይ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የጅማ አባጅፋር ተጫዋች የሆነው ሲዲቤ አንድ ዓመት በክለቡ ከቆየ በኋላ ወደ ባህር ዳር ከተማ በማቅናት የእግርኳስ ህይወቱን ቀጥሏል። በቀጣይም በሲዳማ ቡና ቤት ለአንድ ዓመት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል።

©ሶከር ኢትዮጵያ